- 01 July 2011
ካልተናገረውና ሚስጥሩን ካላዋየው ሌላ በገሐድ የሚታወቅ ሦስት ችግሮች የነበሩበት ግለሰብ እፎይ ለማለት በትግል ላይ ነበር ። ይህ ሰው ከጭንቀቱ የተነሳ ናላው ዞሮ እንቅልፍ በማጣት ሰንበትበት ብሏል። ካጋጠሙት ችግሮች የተነሳ ከዚህ ዝብርቅርቅ ሁኔታ እንዴት ሊወጣ እንደሚችል በማሰብ ሲያወጣና ሲያወርድ ሌሊቱ አልፎበታል። በዚህም ምክንያት ከራሱ ጋር መነጋገርና መቆዘም የዘወትር ተግባሩ አደረገው።
- 22 April 2011
ከሌለህ ምን ልትሰጥ ትችላለህ? ተብዬ ብጠየቅ መልሱ ምንም ነው። እንኳን ልሰጥ ለራሴም የለኝም። ስለዚህ አያስጨንቀኝም። የሚያስጨንቀው የሌለኝ ሆኜ እንዳለኝ ስሆን፣ ወይም እያለኝ እንደሌለኝ ራሴን ስቆጥር ነው። አለበለዚያ በይሉኝታ ሳይኖረኝ በአፌ ቃል ኪዳን ስታሰር ነው። ስለዚህ ካለን እንዳለን፣ ከሌለን እንደሌለን አውቀን ለእግዚአብሔር ራሳችንን በመተው መንፈሳችንን ማሳረፍ ይገባናል። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ያለንና የሚያስፈልገንን ያውቃል።
- 21 February 2011
መንገድህ ላይ ሆኖ ጠልፎና ጠላልፎ የሚያስቀር ደንቃራ ነገር ሁሉ ከታቀደልህ የሕይወት ዓላማ ስለሚያደናቅፍ የታሰበው እንዳይሳካ ያደርጋል። ጥልፍልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ወይም ማምለጫ መንገድ ካልተገኘ በቀር ወደ ሌላ ችግር እንደሚከት የተረጋገጠ ነው። በመጠላለፍ የተነሳ ከዓላማ መውደቅ አለ።
- 21 February 2011
መንገድህ ላይ ሆኖ ጠልፎና ጠላልፎ የሚያስቀር ደንቃራ ነገር ሁሉ ከታቀደልህ የሕይወት ዓላማ ስለሚያደናቅፍ የታሰበው እንዳይሳካ ያደርጋል። ጥልፍልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ወይም ማምለጫ መንገድ ካልተገኘ በቀር ወደ ሌላ ችግር እንደሚከት የተረጋገጠ ነው። በመጠላለፍ የተነሳ ከዓላማ መውደቅ አለ።
- 04 May 2012

ካለፈው የቀጠለ …
ትዕዛዝ ተቀብሎ ከሚወደው አባት፤
ድንገት ቢጠፉበት የአህያ አባላት፤
ከቤቱ ወጣና በቅጽበት፤
እንዲደርስላቸው ከመዓት፤
ከጅብ ከአራዊት ጥፋት፤
ከሆድ ዝርጠጣ የቁም ሞት።
- 04 May 2012
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ
በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ
በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ
እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ!
- 24 April 2012
በሰማይና በፊትህ ብበድልም፤
ወደ ፊትም ልጅህ ልባል ባይገባኝም፤
አንተ ግን ዛሬም አልተውከኝም።
እጅህን ዘርግተህ ተቀበልከኝ
ከሁሉ የተሻለ ልብስ አለበስከኝ
- 13 December 2011

እጅግ ያስገርማል
ይደንቃል ያስደንቃል
የአምላክ ሥራ
አያልቅ ቢወራ ቢወራ።
........................................ የፍጥረትን ሥርዓት ሰማይና ምድሩ፣
........................................ ስድስት ቀን ሲያዘጋጅ ሁሉንም ከሥሩ፣
........................................ ከአእምሮ በላይ ነው ያምላክ አሠራሩ
........................................ ይገርማል አደራረጉ፤ አወቃቀሩ።








Dawit Endelibie Yetebalebet Mistir Mendnew? Part 2




